Skip to main content

KingCounty.gov is an official government website.

Official government websites use .gov
Website addresses ending in .gov belong to official government organizations in the United States.
Secure .gov websites use HTTPS
A lock or https:// means you've safely connected to the .gov website. Only share sensitive information on official, secure websites.

መመሪያዎች ለየማመልከቻ ክፍያዎችን ለመተው እንቅስቃሴና ትእዛዝ

በፍትሀብሄር ወይም በቤተሰብ ሕግ ፍርድ ቤት ክስዎ ውስጥ የፍትሀብሄር ክፍያ እና ተያያዥ ክፍያዎችን መክፈል አልችልም ብለው የሚያምኑ ከሆነ ፍርድ ቤቱ እንዲተውልዎ መጠየቅ ይችላሉ። የማስመዝገቢያ ክፍያ መተው አለበት የሚለውን ለመወሰን ፣ ፍርድ ቤቱ የመክፈል ችሎታዎን ከግምት ውስጥ ያስገባል። ይህን በሚያደርግበት ሁኔታ፣ ፍርድ ቤቱ በፌዴራል ድህነት ደረጃ 125% መሠረት የገንዘብ ተገኝነት ሰንጠረዥን ሊያመለክት ይችላል (ከዚህ በታች ይመልከቱ)። በቤተሰብ ሕግ ጉዳይ ውስጥ የጋራ አቤቱታ ካለ፣ ለክፍያ ማቋረጥ ብቁነትን በሚወስኑበት ጊዜ ገቢዎ ከባለቤትዎ ገቢ ጋር ይጨመራል።

ሆኖም፣ ገቢዎ ከዚህ በታች ካሉባቸው መጠን በላይ ከሆነ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ፍ/ቤቱ መስፈርቶችን ሊያስቀርልዎት ይችላል፣ ነገር ግን እርስዎ መክፈል የማይችሉባቸው ተደጋጋሚ መሰረታዊ የኑሮ ወጪዎች እንዳሉዎት ከተገነዘበ፣ ክፍያዎቹን ወይም ይህን ለማድረግ ሌሎች አስገዳጅ ሁኔታዎች እንዳሉ ካወቀ ክፍያዎቹን ሊተው ይችላል። ብቃት ባለው የሕግ አገልግሎት አቅራቢ የሚወክሉ ከሆነ፣ ያ አቅራቢው ለእነሱ ጥቅም ላይ የዋሉትን ቅጾች በማቅረብ የክፍያ ነፃነትን ሊያገኝ ይችላል።

የቤተሰብ መጠን 1 2 3 4 5 6 7 8 9 ወይም ከዛ በላይ
ከፍተኛ ወርሀዊ ገቢ* $1,663 $2,254 $2,846 $3,438 $4,029 $4,621 $5,213 $5,804 ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰው $592 ይጨምሩ
ከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ* $19,950 $27,050 $34,150 $41,250 $48,350 $55,450 $62,550 $69,650 ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰው $7,100 ይጨምሩ

* “ገቢ” ማለት ግብሮች እና የሕፃናት እንክብካቤ ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የደረሰዎት የተጣራ ገቢ ማለት ነው።

በአሁኑ ጊዜ በርዳታ ፈላጊነት የእርዳታ መርሃግብር ውስጥ እንደሚከተሉ ያሉ የችግርተኞችን ጥቅማጥቅሞችን የሚያገኙ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ክፍያዎቹን ሊተው ይችላል።

  • የፌዴራል ጊዜያዊ ድጋፍ ለተቸገሩ ቤተሰቦች (TANF)
  • ሥራ አጥ ለሆኑ ግለሰቦች በግዛቱ የተሰጠ አጠቃላይ ድጋፍ (GA-U ወይም GA-X)
  • የፌዴራል ተጨማሪ ደህንነት ገቢ (SSI)
  • ከፌዴራል ድህነት ጋር የተዛመዱ የአርበኛ ጥቅማጥቅሞች
  • የራሽን እደላ ፕሮግራም (FSP)

ክፍያዎችን ለማስቀረት ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዳቸውንም የሚጠቀሙ ከሆነ፣ እባክዎ የቅርብ ጊዜ የጥቅማጥቅሞች የሚሰጡበት ደብዳቤ ቅጂ ያሉ ማስረጃዎችን ይዘው ይምጡ።

የሚጠቀሟቸው ቅጾች: 

ፍርድ ቤቱ የክፍያ ማስቀሪያዎችን ለማግኘት መደበኛ ቅጾች አሉት፣ ምንም እንኳን ተመሳሳይ ቅጾችን በሌላ ቦታ ቢያገኙም ሊጠቀሙባቸው ይገባል። ቅጾቹ ያለ ምንም ወጪ በጸሃፊው ጽህፈት ቤት (E609) ወይም በመስመር ላይ (www.courts.wa.gov/forms/?fa=forms.contribute&formID=87) ይገኛሉ፡፡

  1. የሲቪል ክፍያዎችንና ተጨማሪ ክፍያዎችን ለመተው የቀረበ ሃሳብና ትእዛዝ
  2. የገንዘብ መግለጫ (በአሁኑ ጊዜ የሚረዱ፣ ከላይ በተጠቀሰው መሠረት የችግርተኞችን ጥቅማጥቅሞችን የሚያገኙ ከሆነ ፣ ይህንን ቅጽ ማጠናቀቅ አያስፈልግዎትም)

መመሪያዎች፡

ትእዛዙ እንዲካተት ለማድረግ ሁሉንም ቅጾች ሙሉ በሙሉ ይሙሉ። ፍርድ ቤቱ የትእዛዝ-መልቀቂያ ክፍያን አይሞላም፡፡ የቀረበውን ሃሳብና ትእዛዙን መፈረም እና ቀን መጻፍዎን ያረጋግጡ እንዲሁም "የፋይናንስ መግለጫ" ቅጹን መሙላት ወይም የቅርብ ጊዜ ጥቅማጥቅም የተቆረጠልዎን ደብዳቤ ቅጂ ማግኘትዎን ያረጋግጡ፡፡ እንዲሁም ጉዳይዎን ለመጀመር ዋውና ሰነዶች ያስፈልግዎታል፡፡ ለመጀመር የሚያስፈልጉ ሰነዶች (ለምሳሌ፡ አቤቱታዎች፣ ቅሬታዎችና የጉዳይ ምደባ ቦታ ቅጽ እንዲሁም የጉዳይ ማውጫ ሽፋን ወረቀቶች፣ ሚስጥራዊ መረጃ ቅጽ) አብዛኛዎቹ ቅጾች በ https://kingcounty.gov/en/dept/dja/courts-jails-legal-system/court-forms-document-filing/forms ላይ እንዲሁም የቤተሰብ ህግ ቅጾች በ http://www.courts.wa.gov/forms/?fa=forms.static&staticID=14 ላይ ይገኛሉ፡፡

ኮሚሽነሩ ትዕዛዙን ከፈረሙ ምንም ክፍያ ሳይከፍሉ ክስዎን ፋይል ማድረግ ይችላሉ። እንዳይከፍል መደረጉ ከተከለከለ ክስዎን ለማስገባት የማመልከቻ ክፍያውን እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ። ተቀባይነት ካገኘ፣ ጸሃፊው ጉዳይዎን የሚጀመር ሲሆን በሽፋን ወረቀትዎ ላይ ባመለከቱበት መንገድ የሚተገበር ከሆነ የጸደቀውን ትእዛዝ፣ የጉዳይ ቁጥርና የጉዳይ መርሐግብር ቅጂ የሚልክልዎት ይሆናል፡፡ የሚከለከሉ ከሆነ ጸሃፊው የክልከላውን ግልባጭ በሽፋን ወረቀቱ ላይ በተጠቀሰው ዘዴ የሚመልስና ዋና ሰነዶችዎን በፖስታ ይልካል፡፡

በአካል ወይም በፖስታ ከታች በአንዳቸው ቦታ መስጠት

King County Superior Court
Attn: Clerks Office
516 Third Avenue RoomE609
Seattle, WA 98104-2386

የማልግን የክልላዊ የፍትሕ ማዕከል፡
(Maleng Regional Justice Center)
Attn: Clerks Office
401 Fourth Avenue N, Room 2C
Kent, WA 98032

የኪንግ ካውንቲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጸሃፊ ጽህፈት ቤት ከ 8፡30 ኤኤም - 4፡30 ፒኤም ክፍት ሲሆን ይህም ከ 12፡15 - 1፡15 ፒኤም ባለው ሰአት ውስጥ የተገደበ አገልግሎት ይኖረዋል፡፡

በኤሌክትሮኒክ መንገድ መላክ

እንዴት “ከክፍያ ነጻ የሆነ ጉዳይን ማስጀመር” የሚለውን መመሪያ በ https://kingcounty.gov/en/dept/dja/courts-jails-legal-system/courts-financial/fees-payments/fee-waiver ገጽ ላይ ባለው የጸሐፊዎቹ “ክፍያና ክፍያ ማስቀረት” ገጽ ላይ ይገኛል፡፡

ይህን ትርጉም በተመለከተ አስተያየት ስለሰጡን እናመሰግናለን።