የከፍተኛ ፍርድ ቤትና የጸሐፊ ቢሮ የክፍያ መረጃ
ስለ
የክፍያ መጠን፡
ከማመልከቻ ጋር ለተያያዙ ክፍያዎች፣ ቅጂዎችንና ሌሎች የጸሐፊ አገልግሎቶችን ማግኘት፣ ከዚህ በታች ያለውን "የክፍያ መርሐግብር ዝርዝር" ይመልከቱ፡፡ በክፍያው ርእስ ላይ ጠቅ በማድረግ የወጪዎችን ዝርዝርና የክፍያውን መጠን የሚፈቅደውን ህጋዊ ማጣቀሻ ይመልከቱ፡፡ ወይም የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የ PDF ቅጂ ያውርዱ፡ Amharic - አማርኛ
የሚፈጸምበት ክፍያ:
ተቀባይነት ስላላቸው የመክፈያ ዘዴዎች መረጃ ለማግኘት "የሚፈጸም ክፍያ መረጃ" ማውጫን ጠቅ ያድርጉ፡፡
የማስለቀቂያ ክፍያ፡
ተቀባይነት ስላላቸው የመክፈያ ዘዴዎች መረጃ ለማግኘት "የሚፈጸም ክፍያ መረጃ" ማውጫን ጠቅ ያድርጉ፡፡
ያግኙን፡
ለእርዳታ፣ የጽፈት ቤቱ ሰራተኛን በስልክ (206-296-9300, TTY: 206-296-0100)፣ በኢሜል (DJA.CustomerServiceEmail@kingcounty.gov) ወይም ከሶስቱ የጸሐፊ ቢሮ አካባቢዎች አንዱ የሕዝብ ተቆጣጣሪ ሊረድዎት ይችላል ፡፡
የሚፈጸምበት ክፍያ መረጃ
የክፍያ መረጃ፡
- በአካል የተከፈሉ ክፍያዎችና አገልግሎቶች በጥሬ ገንዘብ፣ በቼክ ወይም በገንዘብ ማዘዣ፣ በክሬዲት ወይም በዴቢት ካርድሊፈጽሙት ይችላሉ፡፡ በፖስታ የሚላኩ ክፍያዎች በቼክ ወይም በገንዘብ ማዘዣ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቼኮች በዋሽንግተን ስቴት ባንክ የከፋዩ ስምና አድራሻ በቼኩ ላይ መስፈር ይኖርበታል፡፡ ቼኮችና የገንዘብ ማዘዣዎች ለ "ጸሐፊው"መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡
- በኢንተርኔት መስመር ላይ ለሚደረጉ የማመልከቻና አገልግሎቶች ክፍያዎች በኤሌክትሮኒክ ቼክ ወይም በክሬዲት ካርድ መደረግአለባቸው፡፡ አገልግሎት ልውውጡ ክፍያ በኤሌክትሮኒክ ክፍያዎች ላይ እንደሚተገበር ይወቁ፡፡
- በሕጋዊ የፋይናንስ ግዴታዎች ላይ ክፍያዎችን በተመለከተ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ ፡፡
የማስለቀቂያ ክፍያ መረጃ
ይህ ገጽ ክፍያ ማስቀረት ወይም መቀነስ የሚቻልባቸውን ርእሰ ጉዳዮችን ይዟል፡፡
የማመልከቻ ክፍያዎች
የሚከተሉት መመሪያዎችና ቅጾች ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት በሲቪልና በቤተሰብ ህግ የፍርድ ቤት ጉዳዮች ላይ የማመልከቻ ክፍያዎችን ለመጠየቅ ነው፡፡
መመሪያዎች፡
- የፋይል ማስለቀቂያ ክፍያ
- ብቁ ለሆኑ የህግ አገልግሎት አቅራቢዎች (QLSP) በ APR 8(e)(2) በተገለጸው መሰረት (የተገናኙ ገጾች አልተተረጎሙም፡፡)
- በማስለቀቂያ ክፍያ አዲስ ጉዳይ ይጀምሩ (የተገናኘው ገጽ አልተተረጎመም፡፡)
ቅጾች (የተገናኙ ገጾች አልተተረጎሙም፡፡)፡
ቅጾቹ ያለ ምንም ወጪ በጸሐፊው ጽሕፈት ቤት ወይም በቤተሰብ ሕግ አመቻች ቢሮ (Seattle ሲያትል ፍርድ ቤት፡. W-382፣ በኬኔት የሚሌንግ ክልላዊ የፍትሕ ማእከል፡ 3-D) እና በዋሽንግተን ፍርድ ቤቶች ድህረገጽ፡ www.courts.wa.gov (በቀጥታ፡ ቅጾች፡ አጠቃላይ ህግ 34 የሲቪል ማመልከቻ ማስለቀቂያ ክፍያዎችንና ተጨማሪ ክፍያዎችን መጠየቂያ)፡፡
የጸሐፊ ክፍያዎች
በጸሐፊውና የተፋጠኑ ክፍያዎች ለአንድ ወገን የጸሐፊ ክፍያ መቋረጥን ለመጠየቅ መመሪያዎች አንብበው ቅጹን (ቅጾቹን) ይሙሉ ፡፡ የጸሃፊው ጽሕፈት ቤት የመልከቂያ ክፍያ ጥያቄ
ቅሬታ-የማያስተናግድ ደረሰኝ በስህተት እንደደረሰዎት ካመኑና በማስታወቂያዎ ላይ ስሙንና ቁጥሩ ከተገለጸው ሰራተኛ ጋር አስቀድመው ከተነጋገሩ ይግባኝ ቅጹን ማስገባት ይችላሉ፡ ቅሬታ-የማያስተናግድ የክፍያ ይግባኝ ቅጽ
የቤተሰብ ፍርድ ቤት አገልግሎት ክፍያዎች (የተገናኙ ገጾች አልተተረጎሙም፡፡)
- የወላጅ ሴሚናር፡ ለበለጠ መረጃ በዚህ ይደውሉ፡ Seattle (ሲያትል) 206-477-1464 or Kent (ኬኔት)206-477-2745.
- የቤተሰብ ህግ አመቻች ፕሮግራም: ለማስለቀቂያ ክፍያ መረጃ፣ ወደ ቢሮው ይደውሉ (ሲያትል፡)206-477-2553 ወይም (ኬኔት) 206-477-2781.
የአስተርጓሚ አገልግሎቶች
የትርጉም አገልግሎቶች (የተገናኘው ገጽ አልተተረጎመም፡፡) ለሁሉም የፍርድ ቤት ዝግጅቶች ያለምንም ወጪ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ ከአፍጋኒ እስከ ዙሉ፣ King County የኪንግ ካውንቲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአስተርጓሚ አገልግሎት ቢሮ (OIS) እንግሊዘኛ ያልሆኑ ሰዎችን በፍርድ ቤት ጉዳዮች ለመርዳት ከ140 በላይ ቋንቋዎች አስተርጓሚዎችን ያገኛል፡፡
የክፍያ ማቋረጫ ህጎች እና ደንቦች (የተገናኙ ገጾች አልተተረጎሙም፡፡)
- የፓስፊኪ ሰሜን ምእራብ የፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ደንብ 34: በአቅም ማነስ በሲቪል ጉዳዮች የፍርድ ቤትና የጸሐፊ ክፍያዎችንና ወጪዎችን መተው፡፡
- RCW 36.18.022: የማመልከቻ ክፍያ ሊቀር ይችላል - መቼ፡፡
- King County የኪንግ ካውንቲ የአካባቢ ሲቪል ደንብ 40.1፡ የተናጠልና የውርስ ግልባጭ መምሪያ፡፡
Translate