የህግ የፋይናንስ ካሳ ግዴታዎች ፕሮግራም
በሕግ የሚወሰኑ የገንዘብ ግዴታዎች(LFO)
- ካሳ ማለት በወንጀሉ ምክንያት ጉዳት ላጋጠማቸውና እና/ወይም ያጡት ነገር ካለ ወይም በንብረት ላይ ጉዳት ለደረባቸው ተጎጂዎችን ለማካካስ በፍርድ ቤት የሚከፈል ወጪ ነው፡፡
- ካሳ-ያልሆነ LFO በፍርድ ቤት የታዘዘ ክፍያዎችና ቅጣቶች ናቸው፡፡ በአብዛኛው የተለመዱት ክፍያዎችና ቅጣቶች የተጎጂዎች ቅጣት ግምገማና የ DNA መረጃ ቋት ክፍያዎች ናቸው፡፡ ሌሎች አካላት ሊያካትቱ የሚችሉት እንደ የፍርድ ቤት ወጪዎች፣ የመከላከያ ወጪዎች ወይም የዳኝነት ክፍያዎች ያሉ ነገሮችን ነው፡፡
- ወለድ በ LFO ላይ ከፍርዱ ጀምሮና በእስር ቤት ጊዜ ውስጥ በሙሉ ወይም ርእሰመምህሩ ሙሉ በሙሉ እስኪከፈል ድረስ፡፡ አሁን ያለው መጠን በአመት 12% ነው፡፡
- የመሰብሰቢያ ክፍያዎች ሊጨመሩ ይችላሉ፡፡
LFO የካሳ ፕሮግራም ሰራተኞች
የ LFO የካሳ ፕሮግራም ሰራተኞች ከፍተኛውን የካሳ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ይጥራሉ፡፡ ተከሳሾች የእዳቸውን ሁኔታ እንዲያውቁትና ተጎጂዎች በፍርድ ቤት የተወሰነላቸውን ካሳ በተቻለ ፍጥነት እንዲያገኙ እንሰራለን፡፡
የፕሮግራም ተግባራት
በኪንግ ካውንቲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል በአዋቂዎች የወንጀል ፍርድ ላይ በፍርድ ቤት የታዘዙ የ LFO ክፍያዎች ላይ እቅድ ማድረግና የካሳውን መከታተል፡፡
የፕሮግራሙ ጥቅሞች
- በጉዳት የተነሳ የሚኖር ካሳ፡፡
- ለሌሎች ፕሮግራሞች ጥቅም የሚሰጡ የካሳ ገንዘቦች (ማለትም የወንጀል ተጎጂዎች፣ የመድኃኒት ገንዘብና የፍርድ ቤት ወጪዎች)፡፡
- የተሻሻለ የክፍያና ሌሎች የተገለጹ ውሎችን ማክበር፣ በዚህም የተሳካ ዳግም የመግባት እድሎችን ማሻሻል ያስችላል፡፡
ተጎጂዎች፡ ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች
- መልሶ የማሰባሰብ ኃላፊነት የሚኖርበት ማነው?
- የማረሚያ ቤቱ መምሪያ (DOC) ተከሳሹ በ DOC ቁጥጥር ስር ወይም በ DOC እስር (ማረሚያ ቤት) ላይ እያለ ህጋዊ የገንዘብ ግዴታዎችን (LFO) የመሰብሰብ ሃላፊነት አለበት፡፡ በእስር ላይ እያሉ ገንዘቡ የ LFO እዳ ባለበት ተከሳሽ የመተማመኛ ሒሳብ (Trust Account) ላይ ከተቀመጠ DOC አብዛኛውን ጊዜ ለLFO ክፍያ ከተቀማጭ ገንዘብ 20% ተቀናሽ ያደርጋል፡፡
- ተከሳሹ ከክትትል እና/ወይም ከእስር ከተለቀቀ በኋላ የጸሃፊው ጽህፈት ቤት የመሰብሰብ ሃላፊነት አለበት፡፡
- ተከሳሹ ለተጠቂው ሰው የካሳ ክፍያዎችን በቀጥታ ይከፍላል?
- አይ፣ ተከሳሹ የካሳ ክፍያዎችን በቀጥታ ለጸሐፊው ጽህፈት ቤት ገቢ ያደርጋል፡፡ የጸሐፊው ጽህፈት ቤት ለተጎጂው ቼክ በማዘጋጀት በፖስታ ይልካል፡፡ ይህ ሂደት በርካታ ሳምንታት ሊወስድ ይችላል፡፡
- ካሳዬን ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?
- ምንም እንኳን ካሳው ፍርድ ቤት በኩል ውሳኔ የሚሰጥበት ወይም የቅጣት አንድ አካል ሊሆን ቢችልም ተጎጂዎች ክፍያውን የማግኘት ዋስትና አይኖራቸውም፡፡ ክፍያዎች ተከሳሹ ባለው የገንዘብ ምንጭ ልክ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ወንጀል ከተፈጸመ በኋላ ካሳውን ማግኘት በስሜት፣ በአካልና በገንዘብ ለማገገም ለሚሞክሩ ተጎጂዎች ረጅምና ተስፋ አስቆራጭ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል፡፡
- ከተከሳሹ የተገኘው የካሳ ክፍያ ጸሐፊው ከተቀበለ በኋላ በመደበኛነት በ 15 ቀናት ውስጥ የሚደርስ ይሆናል፡፡ ብዙ ተጎጂዎች በመኖሩ ጊዜ ክፍያው በሚከፈልበት ጊዜ ለእያንዳንዱ ተጎጂ የሚከፈለው መጠን የሚገመገም ይሆናል፡፡
- ጸሃፊው ለእያንዳንዱ ተጎጂ ከ $10.00 ዶላር በታች ቼኮች አይሰጥም ምክንያቱም ይህ ከዚኮኖሚመዊ ሁኔታ አንጻር የማይቻል በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ጸሃፊው ተጨማሪ የክፍያ መጠን እስኪኖር ድረስ ይጠብቃል፡፡ በተቻለ ፍጥነት ክፍያዎች ለመላክ የጸሐፊው ቢሮ ትክክለኛ የሆነ አድራሻዎ እንዲኖሩት ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
- እንደ ተጎጂ፣ አድራሻዬን ወይም ስሜን በፍርድ ቤት በኩል እንዴት ማሻሻል እችላለሁ?
- የአድራሻዎን ወይም የስም ለውጥዎን ለጸሐፊው ጽህፈት ቤት ሰነድ አስደግፈው ማቅረብ ይኖርብዎታል፡፡ ማውረድ የሚቻሉ መመሪያዎች እዚህ ይገኛሉ፡፡
- ተከሳሹ ክፍያውን መፈጸም ካልቻለ ምን ይሆናል?
- ተከሳሹ የገንዘብ አቅም የሚኖረው ከሆነና ክፍያውን በወቅቱ ሳይፈጽም ከቀረ የተወሰዱት እርምጃዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በነዚህ ላይ ብቻ የሚወሰኑ አይሆንም፡ 1) ጌጣጌጥ ወይም ከደሞዝ ወይም ሌሎች ንብረቶችን ማያያዝ፣ 2) የንብረት ባለቤትነት መብት፣ 3) በፍርድ ቤት መቆም የሚያስከትል ጥሰት ማስታወቂያና 4) ተጎጂው በራሱ/በእራሷ ካሳውን የማግኘት መብት አለው (ከዚህ በታች ይመልከቱ)፡፡
- በራሴ ካሳውን ለማግኘት መከታተል ብፈልግስ?
- የፍትሐብሔር ፍርድ በተሰጠበት ሂደት ከተከሳሹ ካሳውን ለማግኘት ክትትል ማድረት ይችላሉ፡፡ ይህ ተጎጂ እንደመሆንዎ መጠን የእርስዎ መብት ነው፡፡ ሁሉም የተሰበሰቡት ገንዘቦች ለተጎጂዎች እንዲከፋፈል ለማድረግና የሒሳብ መዝገቦችን በትክክል ለመያዝ በፍርድ ቤት መዝገብ ቤት ውስጥ መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
ተከሳሾች፡ ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች
- የክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ አላገኘሁም፡፡ ምን ማድረግ ይገባኛል?
- የእርስዎን የአሁን አድራሻ እንዳለን ለመመልከት የ LFO ካሳ አገልግሎት ሰራተኛን ያነጋግሩ፡፡ ወርሃዊ ክፍያዎችን የመፈጸም ሃላፊነት ያለብዎትና መግለጫ ባይደርስዎትም እንኳ መክፈልዎን ማስታወስ ይኖብዎታል፡፡ በየሶስት ወሩ ወደሚታወቁት የመጨረሻ አድራሻዎ መግለጫዎቹ ይላካሉ፡፡ እያንዳንዱ መግለጫ ለመላኪያ ክፍያ (ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት አንድ) ሶስት ሮዝ ፖስታዎችን ይይዛል፡፡
- በእኔ የክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ ወይም በደብዳቤ አለብኝ ብዬ ካሰብኩት እዳ በላይ ያለ የሚመስለው ለምንድነው?
- ከጥፋተኝነት በኋላ በተደረገ ችሎት ካሳ እንዲከፍሉ ታዘው ይሆናል፡፡ ከውሳኔ ቀን ጀምሮ የተወሰነው መጠን ሙሉ በሙሉ እስኪከፈል ድረስ LFO በአመት 12% ወለድ ይሰበስባል፡፡ የመሰብሰቢያ ክፍያ ሊጨመር ይችላል፡፡ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በተሰጠው ትእዛዝ ውስጥ ወጪዎችን ሊጨምር ይችላል፡፡
- አአብረው የተከሰሱት እኩል ድርሻቸውን የማይከፍሉት ለምንድነው?
- በአጠቃላይ ሁሉም አአብረው የተከሰሱት ሙሉ በሙሉ እስኪከፈሉ ድረስ ለጠቅላላ እዳው መጠን ተጠያቂ ናቸው፡፡
- የክፍያ እቅድ ማዘጋጀት እችላለሁ?
- አዎ፣ በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች ይቻላል፡፡ አሁን ያለውን ገቢዎን መሰረት በማድረግ የክፍያ እቅዱ እንዲስተካከል ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ እርስዎን የሚረዳዎትን የ LFO ካሳ አገልግሎት ሰራተኛ ይደውሉ (በመጨረሻ ስምዎ መሰረት)፡፡ የገንዘብ መገልጫ ቅት እንዲሞሉና በሚፈለገው ደጋፊ ሰነድ እንዲመልሱ ይጠየቃሉ፡፡ ያለዎት የLFO መጠን ሲቀንስ ለማየት የእርስዎ ወርሃዊ ክፍያ ከወርሃዊ የወለድ ክምችትና ከማንኛውም የካሳ ክፍያዎች በላይ መሆን እንዳለባቸው ያስታውሱ፡፡
- የባንኩን የመስመር ላይ ቢል ክፍያ አገልግሎት በመጠቀም ክፍያዬን መፈጸም እችላለሁ?
- አይደለም፣ ነገር ግን የኤሌክትሮኒክ የገንዘብ ዝውውር (EFT) ሂደትን በመጠቀም ለራስ ሰር ክፍያዎች መመዝገብ ይችላሉ፡፡ ክፍያዎችን በቀጥታ ከባንክ ሂሳብዎ እንዲያወጣ የጸሐፊው ቢሮ መፍቀድ አለቦት፡፡ ይህንን ለማድረግ የራስ ሰር ክፍያ ፈቀዳውን ይሙሉ እና ወደ ጸሐፊው ቢሮ ይመልሱት፡፡
- ክፍያ መፈጸም ባልችልስ?
- ፍርድ ቤቱ በተከታታይ የተደረጉ ወርሃዊ ክፍያዎችን ማየት ይፈልጋል፡፡ ተከታታይ ወርሃዊ ክፍያዎችን መክፈል ሳይችሉ የቀሩ እንደሆን ለጉዳይዎ የተመደበውን የ LFO ካሳ አገልግሎት ሰራተኛ ይደውሉ፡፡
- ጭማሪ ክፍያ ብከፍልስ?
- ከተቀመጠው ገደብ በላይ ክፍያ እንደከፈሉ ከተረጋገጠ የተመላሽ ገንዘብ ቼክ ወጪ ተደርጎ ወደ መዝገብዎ አድራሻ የሚላክ ይሆናል፡፡
- በሂሳቡ የማልስማማ ከሆነ ወይም የጎደሉ ክፍያዎች አሉ ብዬ ብገምትስ?
- ክፍያዎችዎን ከፍርድ ቤት የክፍያ ታሪክ ጋር ማስተያየትና ሒሳብዎ ስህተት ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልግዎታል፡፡ የ"ማስረጃዎች" ምሳሌዎች የፍርድ ቤት ደረሰኞች ወይም የተሰረዘው የገንዘብ ማዘዣ ወይም የገንዘብ ተቀባይ ቼክ የፊትና የኋላው ቅጂ ናቸው፡፡
- የክፍያ ታሪኬን ቅጂ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?
- በአካል፡ በኪንግ ካውንቲ ፍርድ ቤት፣ 516 Third Ave, Room E-609, Seattle ወደሚገኘው የጸሐፊው ቢሮ ይምጡ፡፡ ወደ የሂሳብ ቆጣሪ ይሂዱና የክፍያ ታሪክ ይጠይቁ፡፡ ዋጋው በገጽ 50 ሳንቲም ነው (ጥሬ ገንዘብ ወይም ቼክ ብቻ)፡፡
- በፖስታ፡ የክፍያ ታሪክ በሚጠይቁ ጊዜ የሚከተለውን መረጃ ያካትቱ፡ 1)የጉዳዩ ቁጥር፣ 2)ስምና አድራሻ፣ 3) በጉዳዩ ቁጥር የ $10,00 ተቀማጭ ክፍያ፣ እና 4) በቂ ፖስታ በራሱ አድራሻ ቴምብር ያለው ፖስታ ጥያቄውን ወደሚከተለው ይላኩ፡ የኪንግ ካውንቲ ጸሐፊ ጽሕፈት ቤት፣ ጉዳዩ፡ Accounting, 516 Third Ave, E-609, Seattle, WA 98104
- ክፍያዎች፡ ለእያንዳንዱ የጉዳይ ቁጥር $10.00 ዶላር በማስያዣነት ተቀማጭ ያስፈልጋል፡፡ በዋሽንግተን ስቴት ባንክ ላይ ወጪ የሚደረጉ ቼኮች ብቻና በቼኩ ላይ የሰፈረው የከፋዩን ስምና አድራሻ ጨምሮ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ የዋሽንግተን ስቴት የባንክ ሒሳብ የሌለዎት ከሆነ ተቀማጭ ገንዘብ ለማግኘት በገንዘብ ተቀባይ ቼክ ወይም የገንዘብ ማዘዣ በዩኤስ ፈንዶች መላክ ይችላሉ፡፡ አጠቃላይ የክፍያ ታሪክ ዋጋ ከ$10.00 በታች ከሆነ ትርፍ የመጣው ክፍያው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ለክሬዲት ቢሮዎች ሪፖርት ያደርጋሉ?
- የጸሐፊው ጽህፈት ቤት በቀጥታ ለዱቤ ቢሮዎች ሪፖርት የሚያደርግ ሳይሆን LFOs እንደ የፍትሐብሔር ብይን በፍርድ ቤት መዝገብ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የፍትሐብሔር ብይኖች የሕዝብ መዝገቦች ሲሆኑ በአጠቃላይ በብድር ቢሮዎች የሚወሰዱ ይሆናል፡፡
የክፍያ መረጃ
በአካል ተገኝቶ መክፈል
በጥሬ ገንዘብ፣ በገንዘብ ማዘዣ ወይም በገንዘብ ተቀባይ ቼክ በአካል ተገኝተው መክፈል ይችላሉ፡፡ ምንም የግል ቼኮች የሉም፡፡ የገንዘብ ትእዛዙን ወይም የገንዘብ ተቀባይ ቼክ ለሚከተለው እንዲከፈል ያድርጉ፡ “የኪንግ ካውንቲ ጸሐፊ”
በአካል ለመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ ከ 9፡00 እስከ 4፡30 ከጸሐፊው ቢሮ ስፍራዎች በአንዱ (አቅጣጫ እዚህ) ይመጣል፡፡
በፖስታ መክፈል
በገንዘብ ማዘዣ ወይም በገንዘብ ተቀባይ ቼክ ብቻ በፖስታ መክፈል ይችላሉ፡፡ ምንም የግል ቼኮች የሉም፡፡ የገንዘብ ማዘዣውን ወይም የገንዘብ ተቀባይ ቼኩን ለሚከተሉት ይክፈሉ ለ፡ "የኪንግ ካውንቲ ጸሐፊ"
በገንዘብ ማዘዣው ወይም በገንዘብ ተቀባይ ቼክ ፊት፣ ማተም፡
- የእርስዎ ስም መሆን ያለበት በፍርድ ቤት ትእዛዝ ላይ እንደተገለጸው ነው
- ክፍያ እየፈጸሙ ያሉት እያንዳንዱ የጉዳይ ቁጥር
- ከእያንዳንዱ የጉዳይ ቁጥር ቀጥሎ የሚከፍሉት የዶላር $ መጠን
ደረሰኙ እንዲላክልዎ የሚፈልጉት በፖስታ ከሆነ ከክፍያዎ ጋር በራስ አድራሻና ቴምብር የተደረገ ፖስታ ይላኩ፡፡
ክፍያ በፖስታ የሚላከው ወደ፡
ኪንግ ካውንቲ የፍርድ ቤት ጸሃፊኤ.ቲ.ቲ.ኤን፡- ገንዘብ ያዥ
5163rd. Ave, Room E-609
Seattle, WA 98104
ለ LFO ክፍያ አስታዋሾች ይመዝገቡ
እዚህ ጠቅ ያድርጉ (የተገናኘው ገጽ አልተተረጎመም፡፡) እና ወርሃዊ የጽሁፍ ለመቀበል ወይም የኢሜል ማስታወሻ ለመቀበል ስልክ ቁጥርዎን ወይም የኢሜል አድራሻዎን ያስገቡ፡፡
ዝርዝሩን ወደ የበላይ ፍርድ ቤት ጸሃፊ ቢሮ በመቀየር ይውሰዱናና ለከፍተኛ ፍርድ ቤት - LFO የክፍያ ማስታወሻዎች በሚለው ሳጥን ላይ ምልክት ያድርጉ፡፡
የተከሳሽ አድራሻ ማሻሻያ አስገባ
የ LFO የክፍያ መጠየቂያ አድራሻ ማሻሻያ ቅጽ፡፡ አዲስ የፖስታ አድራሻ ለማቅረብ እዚህ ጠቅ ያድርጉ፡፡ ማስታወሻ፡ የጉዳዩ ቁጥር(ሮች) ያስፈልጋል (ሉ)፡፡
Translate