ግዛት v ብሌክ መረጃ
ስቴት v. ብሌክ ምንድን ነው?
የዋሽንግተን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቅርብ ጊዜ በስቴት v ብሌክ ምክንያት ቁጥር 96873-0 (የካቲት 25/2021) የሰጠው አስተያየት RCW 69.50.4013 እና የቀደሙት ሕጎች (በጋራ “RCW 69.50.4013” ወይም “ቀላል ይዞታ”) ሕገ መንግስታዊ አይደሉም፡፡ ይህ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማስታገስ የሚደረጉ የውሳኔ ሃሳቦች ቁጥር አስከትሏል፡፡
የአደንዛዥ እጽ ወንጀሌን ነጻ ለመሆን ማድረግ የሚኖርብኝ ነገር አለ?
የለም፣ በኪንግ ካውንቲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብሌክ በስቴት v ብሌክ ብይን ተጽእኖ የተከሰቱት ሁሉም የአደንዛዥ እጽ ይዞታ ፍርዶች በአቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት የሚገመገሙና ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ በተሰጠበት ቀን (ከአዲሱ እስከ ትልቁ) መሰረት ለጻ ለማድረግ ትእዛዝ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በእርስዎ ጉዳይ ላይ ትእዛዝ እንደገባ ለማየት እንዲችሉ የጉዳይ ፋይልዎን የጸሐፊው መዝገቦች መግኛ ፖርታልን እዚህ በመጠቀም ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ (የተገናኘው ገጽ አልተተረጎመም፡፡)
ጉዳይዎን ለማግኘት ችግር ካጋጠመዎት በሚከተለው ሊያገኙን ይችላሉ፡
- ኢሜል፡ clerksofficecustomerservice@kingcounty.gov
- ስልክ፡ 206-296-9300
የጥፋተኝነት ላይ የተላለፈው ውሳኔዬ ከተፈታ በኋላ ምን ይሆናል?
ነጻ የማድረጉ ትእዛዝ አንዴ ከገባ ጸሐፊው የፍርድ ቤቱን መዝገብ እንዲዘምን ያደርግና የዋሽንግተን ስቴት ፓትሮል መዝገቦቻቸውን ለማዘመን የትእዛዙን ቅጂ ይልክላቸዋል፡፡
ለተመላሽ ገንዘብ ብቁ መሆን የሚችለው ማነው?
በአንድ ጉዳይ ላይ ብቸኛው ጥፋተኛ (ዎች) አደንዛዥ እጽ ይዞታ ላይ በሚሆንበት ጊዜ ተመላሽ ገንዘቦች ይታዘዛሉ፡፡ ማመልከቻ በጸሐፊው ከተቀበለና ከተፈቀደ በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ የተከፈለ ማንኛውም LFO ለተከሳሹ ሊመለስ ይችላል፡፡
የአደንዛዥ እጽ ክስና ሌላ ማንኛውም የቅጣት ውሳኔ ያላቸው ጉዳዮች በዚህ ሂደት በኩል ገንዘቡ ተመላሽ እንዲሆን ለማድረግ ብቁ አይደሉም፡፡ ገንዘብ ተመላሽ መደረግ አለበት ብለው የሚያምኑ ከሆነ እባክዎን ከጠበቃዎ ጋር ይማከሩ ወይም የህዝብ መከላከያ መምሪያን በዚህ ያግኙ
- ኢሜል፡ DPDBlakeRequest@kingcounty.gov
- ስልክ፡ 206-296-7662 ወይም ነጻ መስመር በ 1-844-935-3534
ተመላሽ ገንዘቡን እንዴት እጠይቃለሁ?
- በእርስዎ ጉዳይ(ዎች) ላይ ጥፋተኝነት ላይ ነጻ መለቀቅ ላይ ትእዛዝ መሰጠቱን ያረጋግጡ፡፡
- ከዚህ ቀደም በጉዳዩ(ቹ) ላይ የ LFO ክፍያ ከፍለው ከሆነ ከዚህ በታች ባሉት ሶስት መንገዶች ገንዘቡ ተመላሽ እንዲደረግ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ኢሜል፡ የተሞላ የማመልከቻ ቅጽና የማንነት ማረጋገጫ ወደዚህ ይላኩ፡ DJA-BlakeRefund@kingcounty.gov
- ደብዳቤ፡ ማመልከቻውን ያውርዱ፣ ያትሙና ይሙሉ፣ የማንነት ማረጋገጫ ያቅርቡና ከታች ባለው አድራሻ ይላኩ፡፡
- በአካል: ማመልከቻውን ለመሙላት እንዲሁም የማንነት ማረጋገጫውን ለማሳየት የእኛን ጽህፈት ቤት ይጎብኙ፡፡
516 Third Avenue, Rm E-609
Seattle, WA 98104
ተመላሹን እንዴት ነው ማግኘት የምችለው?
አንዴ ጸሃፊው የተመላሽ ገንዘብ ማመልከቻን ካጸደቀ፣ ተመላሽ ገንዘቦች በቅድመ ክፍያ ዴቢት ካርድ ወይም በቼክ ይሰጥዎታል። እባክዎን የትኛውን አማራጭ እንደሚመርጡ በማመልከቻው ላይ ያመላክቱ።
የምትፈልገውን ማግኘት አልቻልክም?
ተጨማሪ የስቴት v. ብሌክ መርጃዎችን ይመልከቱ ወይም ጠበቃን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ማወቅ ይኖርብዎታል፡፡ (የተገናኘው ገጽ አልተተረጎመም ነገር ግን ነጻ የትርጉም እገዛ በህዝብ መከላከያ መምሪያ በኩል ይገኛል፡፡)
Translate