የህዝብ የጤና ፈቃድ: መስከረም 2025 የሚመጣ
የህዝብ ጤና የአካባቢ ጤና አገልግሎት ክፍል አዲስ የፈቃድ ስርዓት መጀመሩን ሲያበስር በደስታ ነው፡ የህዝብ ጤና ፍቃድ ማእከል
የፈቃድ ማዕከሉ የፈቃድ ሂደቱን በማቀላጠፍ እና ስለ ማመልከቻዎ መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማድረግ ደንበኞቻችንን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል የተነደፈ ነው።
የፈቃድ ማዕከሉ አገልግሎቶች የሚያካትቷቸው:-
- የምግብ ንግድ ፈቃድ እና እቅድ ግምገማ
- የውሃ መዝናኛ ፋሲሊቲ ፈቃድ እና እቅድ ግምገማ
- የቤት እንስሳት ንግድ ፈቃድ እና እቅድ ግምገማ
- ደረቅ የቆሻሻ መገልገያዎች እና ደረቅ/የህክምና ቆሻሻ ተሽከርካሪ ፈቃዶች
- የቧንቧ እና የጋዝ ቱቦዎች ፍቃድ እና እቅድ ግምገማ
- በቦታው ላይ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ማመልከቻዎች
- የትምህርት ቤት እቅድ ግምገማ
- ደህንነቱ ያልተጠበቀ የምግብ አያያዝ፣ አይጦች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶች እና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎች ቅሬታዎች እና ጥያቄዎች
- እና ሌሎችም!
የህዝብ ጤና ፍቃድ ማእከል ስራ ለመጀመር ገና ወራቶች ቀርተውታል፣ ነገር ግን የተሳለጠ ሽግግርን ለማረጋገጥ ለደንበኞቻችን በቅድሚያ መረጃ እየሰጠን እንገኛለን። ይህንን ድረ-ገጽ በሪሶርሶች፣ መመሪያ እና ወቅታዊ መረጃ እናዘምነዋለን።
ይህን አዲስ ስርዓት እያሰስን ባለንበት ጊዜ ላሳዩት ትዕግስት እናመሰግናለን!
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
የፈቃድ ማእከሉ ለምግብ ንግዶች፣ የውሃ መዝናኛ ተቋማት፣ የቤት እንስሳት ንግዶች፣ የደረቅ እና የህክምና ቆሻሻ መገልገያዎች፣ የቧንቧ እና የጋዝ ቱቦዎች፣ በቦታው ላይ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶች እና ለትምህርት ቤቶች አዲሱ የፈቃዶችና የእቅድ ግምገማ ማመልከቻዎች የኦንላይን አገልግሎት ፖርታል ይሆናል:: እንዲሁም ለሰራተኞቻችን ደህንነቱ ያልተጠበቀ የምግብ አያያዝ፣ አይጦች ወይም ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎች ቅሬታዎችን ወይም ጥያቄዎችን ለማቅረብ ፖርታሉን መጠቀም ይችላሉ።
የፈቃድ ማእከሉ የአሁኑን የአካባቢ ጤና የኦንላይን አገልግሎቶችን ፖርታል/Environmental Health online services portal ይተካል።
እኛ እየተሸጋገርን ነው ምክንያቱም አሁን ካለውና ጊዜው ካለፈበት ሶፍትዌራችን የበለጠ የፈቃድ ማእከሉ የተሻሻለ የደንበኛ ልምድን ከተለያዩ የኦንላይን ባህሪያት ጋር ይሰጣል:: እንዲሁም አሁን ያለን ሲስተም ካሁን በኋላ በሻጩ/ቬንደሩ አይደገፍም::
የቢዝነስ ባለቤቶች እና የማህበረሰብ አባላት የፈቃድ ማእከልን ከታች ለተመለከቱት አዲስ ፈቃዶች፣ የፍቃድ እድሳት እና ለግምገማ እቅድ ይጠቀማሉ፡-
- ለምግብ ንግዶች፣
- ለውሃ መዝናኛ ተቋማት
- ለቤት እንስሳት ንግዶች፣
- ለደረቅ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መገልገያዎች እና ደረቅ እና ባዮሜዲካል ቆሻሻ ማጓጓዣዎች
- ለቧንቧ እና የጋዝ ቱቦዎች፣
- በቦታው ላይ ላለ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶች
- ለትምህርት ቤቶች
እንዲሁም የማህበረሰብ አባላት ስለ አይጦች እና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎች ቅሬታዎችን ወይም ጥያቄዎችን ለማቅረብ የፍቃድ ማእከልን መጠቀም ይችላሉ።
የፈቃድ ማዕከሉ በአሁኑ መስከረም (2025) ይጀምራል:: ጊዜውን በተመለከተ እና ምን እንደሚጠበቅ ወቅታዊ መረጃ በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ እናቀርባለን::
አዲሱ አሰራር እስኪጀመር ድረስ ደንበኞች የአካባቢ ጤና የኦንላይን አገልግሎቶችን ፖርታል/Environmental Health online services portal መጠቀማቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋል::